Beke primary and Middle School
Announcement የ2017ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በትምህርት ቤታችን ተሠጠ

የ2017ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በትምህርት ቤታችን ተሠጠ

27th May, 2025

በቤኬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በከተማ ደረጃ የተዘጋጀውን ሞዴል ፈተና ለተማሪዎች በዛሬው ዕለት እንዲጀምሩ ተደርጓል።

በዕለቱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ በላይ ተገኝተው ማስጀመር ችለዋል።

በዕለቱ የት/ቤቱ ርዕሳነ መምህራኖች ለተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆንላቸውና ተረጋግተው እንዲፈተኑ እራሳቸውን እንዲመዝኑና የራሳቸውን ብቻ በአግባቡ እንዲሰሩ የኩረጃን አስከፊነት አጠር ያለ ገለፃ መስጠት ተችሏል።

ፈታኝ መምህራንም በሰዓቱ የተገኙና አጠር ያለ በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። የፈተናውንም ሂደት የት/ርት ቤቱ የፈተና ኮሚቴዎችና ዩኒት አስተባባሪዎች የማስተባበር ስራ መስራት ችለዋል።የፈተናውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የክላስተሩ ሱፐርቫይዘሮች ምልከታ ማድረግ ችለዋል።በዕለቱ የተማሪዎች ምገባ በመጋቢ እናቶች አማካኝነት በማከናወን ፈተናው በተቀመጠለት ሰዓት ተጠናቋል ።

ግንቦት 19/2017

.

Copyright © All rights reserved.

Created with