Beke primary and Middle School
Announcement የሀገርን እወቅ ክበብ ትምህርታዊ ጉዞ አደረገ

የሀገርን እወቅ ክበብ ትምህርታዊ ጉዞ አደረገ

31st May, 2025

በቤኬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኘው በሀገርን እወቅ ክበብ አማካኝነት ግንቦት 20/2017 ዓ.ም ተማሪዎች የወዳጅነት ፖርክንና የአዲስ አበባ ሙዚየምን መጎብኘት ችለዋል።

ክበቡም በዘንድሮ ዓመት ለተማሪዎች የተዘጋጀውን ትምህርታዊ ጉዞን በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል። ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በአካባቢያቸውና በአቅራቢያቸው ያሉት ነገሮች በመመልከት ከተማሩት ትምህርት ጋር ለማስተሳሰር እንደሚረዳቸው የታወቀ ነው። የክበቡ ተጠሪና አባል መምህራንም ይሄንን ከግምት በማስገባት ከትምህርት ቤቱ አስተዳደርና ከተማሪዎች ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ጉዞውን ማዘጋጀት ተችሏል።

በዕለቱ ለተማሪዎች አስፈላጊውን ጉዞና አቅርቦት በማቅረብ ረገድ ለተሳተፉ መምህራን፤ አስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ምስጋናውን ያቀርባል።

ቤኬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት

.

Copyright © All rights reserved.

Created with